tg-me.com/timhirt_minister/140
Last Update:
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የረቀቀው የአጠቃላይ ትምህርት ህግ የህፃናት የመማር መብትን የሚያረጋግጥ ነው፡- ትምህርት ሚኒስቴር፡፡
------------------------------------------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን የመማር መብትና ትምህርት የመከታተል ግዴታን ያካተተ ረቂቅ ህግ አዘጋጅቷል፡፡
የትምህርት ረቂቅ ህጉ የአጠቃላይ ትምህርት ተሳትፎን በማሳደግ ተማሪዎች አስፈላጊውን መሠረታዊ ዕውቀት፤ ክህሎትና አመለካከት ጨብጠው መልካም ዜጎች እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡
በረቂቅ ህጉ ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ማንኛውም ህጻን በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ትምህርትን በነፃ የመማር መብት እንዳለውና ትምህርቱንም የመከታተል ግዴታ ያለበት ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ደግሞ በነፃ እንዲማር ይደነግጋል፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጁ ወይም የሚያስተዳድረው ልጅ ወደ ትምህርት ቤት የመላክና ትምህርቱን እንዲከታተል የማድረግ ግዴታ እንዳለበት በረቂቅ ህጉ ተመላክቷል፡፡
ተማሪዎች ትምህርታቸውን ያለማቋረጥ መከታተላቸውን ማረጋገጥ ደግሞ የትምህርት ቤቱ ግዴታ ነው፡፡
የህፃናትን የመማር መብት የሚያረጋግጠው ይህ ረቂቅ ህግ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን በሚመለከተው አካል ሲፀድቅ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
BY Sport 360
![](https://photo.tg-me.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/b_cyutMgzCnP2EIOj-JAdlFUXvDbmBek34nJIXHY5g0r_Dwo5uyqV5d16TIQzrZhZfUCO-pTeQ68-DrHfUGccz5fPvXLTa30mzArOxifrKIeFntK6V0uEJ-YPiaOfqw2kZrlCJxp-K2hx8Ed6JrhdEyJ4kWDivl7Hely4fpEJpRYgzOe6K6DKzVjvyoKTgg3NDGV-mgfQtm86BdPYDSdQFg3o_qvJ6KXd_zs8YaRv2-2jpdGWSw6fzFmkDXwvb3wQHxtyCBMN-jaNUecyNqZa_6hHBM4TGhDlyMChF8mDDnTPxv6Q2YPjT9NTBH2r5YMWbKboXcEg_upf33kI735_A.jpg)
Share with your friend now:
tg-me.com/timhirt_minister/140